EndaleWeldegiyorgs ሙላኝ ተቆጣጠረኝ Mulagn Tekotateregn - LYRICS | በግጥም 2024 (Official Video)

Поділитися
Вставка
  • Опубліковано 14 жов 2024
  • ጠልቄ መሄድ እፈልጋለሁ
    የእኔ እርካታ የአንተ ክብር ነው
    ላይ ላዩን መሄድ ይቅርብኝና
    (ይስጠም ሕይወቴ በህልውና) ( 2x)
    መንፈስ ቅዱስ (2x)
    አዝ፦ ሙላኝ ተቆጣጠረኝ
    ሌላ ሕይወት አይኑረኝ (፬x)
    ላንብብ ቃልህን ልስማ ሕግህን
    ላድርግ ስራዬን ደስ የሚልህን
    መቅደስነቴ ለአንተ ብቻ ነው
    የለኝም በአንተ ላይ ደባል የማደርገው
    ከምር ነው ከልብ ነው
    የአንተ መሆን ምፈልገው
    ማንከስ ይቅር በሃሳቤ
    ልከተልህ ቆርጦ ልቤ
    አዝ፦ ሙላኝ ተቆጣጠረኝ
    ሌላ ሕይወት አይኑረኝ (፬x)
    እኔ ግን
    እኔ
    አኔ ግን (2x)
    በጽድቅህ ፊትህን አያለሁ
    ክብርህን ሳይ እጠግባለሁ (2x)
    ቁርጭምጭሚት ጋ ባለው ሕይወቴ
    በቃኝ አልበል በዚህ ረክቼ
    ጉልበቴን እና ወገቤን አልፈህ
    ተቆጣጠረኝ ከሁሉ ልቀህ
    በአንተ ተይዞ ሁሉ ነገሬ
    ቢያልቅ ይሻላል ቀሪ ዘመኔ
    ጠልቄ መሄድ እፈልጋለሁ
    የእኔ እርካታ የአንተ ክብር ነው
    ላይ ላዩን መሄድ ይቅርብኝና
    (ይስጠም ሕይወቴ በህልውናህ) 2x
    መንፈስ ቅዱስ (2x)
    አዝ፦ ሙላኝ ተቆጣጠረኝ
    ሌላ ሕይወት አይኑረኝ (፬x)
    #mezmureproterstant #song #amharicmezmur

КОМЕНТАРІ • 1