አቡቀለምሲስ - የዮሐንስ ራዕይ- Apocalypse 017 - ራዕይ 9፡1-23 የመለከት ፍርዶች (ክፍል 2)
Вставка
- Опубліковано 10 лют 2025
- ምዕራፍ 9
አምስተኛውም መልአክ ነፋ፤ ከሰማይም ወደ ምድር ወድቆ የነበረ ኮከብ አየሁ፥ የጥልቁም ጕድጓድ መክፈቻ ተሰጠው።
2 የጥልቁንም ጕድጓድ ከፈተው፤ ጢስም ከታላቅ እቶን እንደሚወጣ ጢስ ሆኖ ከጕድጓዱ ወጣ ፀሐይና አየርም በጕድጓዱ ጢስ ጨለሙ።
3 ከጢሱም አንበጣዎች ወደ ምድር ወጡ፥ የምድርም ጊንጦች ሥልጣን እንዳላቸው ሥልጣን ተሰጣቸው።
4 የእግዚአብሔርም ማኅተም በግምባራቸው ከሌለባቸው ሰዎች በቀር በምድር ያለውን ሣር ቢሆንም ወይም ማናቸውንም የለመለመ ነገር ወይም ማናቸውንም ዛፍ እንዳይጐዱ ተባለላቸው።
5 አምስትም ወር ሊሣቅዩአቸው ተሰጣቸው እንጂ ሊገድሉአቸው አይደለም፤ እነርሱም የሚሣቅዩት ሥቃይ ጊንጥ ሰውን ነድፎ እንደሚሣቅይ ነው።
6 በዚያም ወራት ሰዎች ሞትን ይፈልጋሉ አያገኙትምም፥ ሊሞቱም ይመኛሉ ሞትም ከእነርሱ ይሸሻል።
7 የአንበጣዎቹም መልክ ለጦርነት እንደ ተዘጋጁ ፈረሶች ነው፥ በራሳቸውም ላይ ወርቅ እንደሚመስሉ አክሊሎች ነበሩአቸው፥ ፊታቸውም እንደ ሰው ፊት ነበረ፤
8 የሴቶችን ጠጕር የሚመስል ጠጕር ነበራቸው፥ ጥርሳቸውም እንደ አንበሳ ጥርስ ነበረ፥
9 የብረት ጥሩር የሚመስልም ጥሩር ነበራቸው፥ የክንፋቸውም ድምፅ ወደ ጦርነት እንደሚጋልቡ እንደ ብዙ ፈረሶች ሰረገላዎች ድምፅ ነበረ።
10 እንደ ጊንጥም ጅራት ያለ ጅራት አላቸው በጅራታቸውም መውጊያ አለ፥ ሰዎችንም አምስት ወር እንዲጐዱ ሥልጣን አላቸው።
11 በእነርሱም ላይ ንጉሥ አላቸው እርሱም የጥልቅ መልአክ ነው፥ ስሙም በዕብራይስጥ አብዶን በግሪክም አጶልዮን ይባላል።
12 ፊተኛው ወዮ አልፎአል፤ እነሆ፥ ከዚህ በኋላ ገና ሁለት ወዮ ይመጣል።
13 ስድስተኛውም መልአክ ነፋ፤ በእግዚአብሔርም ፊት ካለ በወርቅ ከተሠራ መሠዊያ ቀንዶች አንድ ድምፅ ሰማሁ፥
14 መለከትም ያለውን ስድስተኛውን መልአክ። በታላቁ ወንዝ በኤፍራጥስ የታሰሩትን አራቱን መላእክት ፍታቸው አለው።
15 የሰዎችንም ሲሶ እንዲገድሉ ለሰዓቱና ለቀኑ ለወሩም ለዓመቱም ተዘጋጅተው የነበሩ አራቱ መላእክት ተፈቱ።
16 የፈረሰኞችም ጭፍራ ቁጥር እልፍ ጊዜ እልፍ፥ እልፍ ጊዜ እልፍ ነበረ፤ ቁጥራቸውን ሰማሁ።
17 ፈረሶቹንና በእነርሱም ላይ የተቀመጡትን እንዲሁ በራእይ አየሁ፤ እሳትና ያክንት ዲንም የሚመስል ጥሩር ነበራቸው፤ የፈረሶቹም ራስ እንደ አንበሳ ራስ ነበረ፥ ከአፋቸውም እሳትና ጢስ ዲንም ወጣ።
18 ከአፋቸውም በወጡት በእሳቱና በጢሱ በዲኑም በእነዚህ ሦስት መቅሰፍቶች የሰዎቹ ሲሶ ተገደለ።
19 የፈረሶቹ ሥልጣን በአፋቸውና በጅራታቸው ነውና፤ ጅራታቸው እባብን ይመስላልና፥ ራስም አላቸው በእርሱም ይጐዳሉ።
20 በእነዚህም መቅሠፍቶች ያልተገደሉት የቀሩቱ ሰዎች ለአጋንንትና ያዩ ወይም ይሰሙ ወይም ይሄዱ ዘንድ ለማይችሉ ከወርቅና ከብር ከናስም ከድንጋይም ከእንጨትም ለተሠሩ ለጣዖቶች እንዳይሰግዱ ስለ እጃቸው ሥራ ንስሐ አልገቡም፤
21 ስለ መግደላቸውም ቢሆን ወይም ስለ አስማታቸው ወይም ስለ ዝሙታቸው ወይም ስለ ስርቆታቸው ንስሐ አልገቡም።
በዙፋኑ ላይም በተቀመጠው በቀኝ እጁ ላይ በውስጥና በኋላ የተጻፈበት በሰባትም ማኅተም የተዘጋ መጽሐፍን አየሁ።
2 ብርቱም መልአክ። መጽሐፉን ይዘረጋ ዘንድ ማኅተሞቹንም ይፈታ ዘንድ የሚገባው ማን ነው? ብሎ በታላቅ ድምፅ ሲያውጅ አየሁ።
3 በሰማይም ቢሆን በምድርም ላይ ቢሆን ከምድርም በታች ቢሆን መጽሐፉን ሊዘረጋ ወይም ሊመለከተው ማንም አልተቻለውም።
4 መጽሐፉን ሊዘረጋ ወይም ሊመለከተው የሚገባው ማንም ስላልተገኘ እጅግ አለቀስሁ።
5 ከሽማግሌዎቹም አንዱ። አታልቅስ፤ እነሆ፥ ከይሁዳ ነገድ የሆነው አንበሳ እርሱም የዳዊት ሥር መጽሐፉን ይዘረጋ ዘንድ ሰባቱንም ማኅተም ይፈታ ዘንድ ድል ነሥቶአል አለኝ።
6 በዙፋኑና በአራቱ እንስሶች መካከልም በሽማግሌዎችም መካከል እንደ ታረደ በግ ቆሞ አየሁ፥ ሰባትም ቀንዶችና ሰባት ዓይኖች ነበሩት እነርሱም ወደ ምድር ሁሉ የተላኩ የእግዚአብሔር መናፍስት ናቸው።
7 መጥቶም በዙፋን ላይ ከተቀመጠ ከዚያ ከቀኝ እጁ መጽሐፉን ወሰደው።
8 መጽሐፉንም በወሰደ ጊዜ አራቱ እንስሶችና ሀያ አራቱ ሽማግሌዎች በበጉ ፊት ወደቁ፥ እያንዳንዳቸውም በገናንና የቅዱሳን ጸሎት የሆነ ዕጣን የሞላበትን የወርቅ ዕቃ ያዙ።
9 -10 መጽሐፉን ትወስድ ዘንድ ማኅተሞቹንም ትፈታ ዘንድ ይገባሃል፥ ታርደሃልና፥ በደምህም ለእግዚአብሔር ከነገድ ሁሉ ከቋንቋም ሁሉ ከወገንም ሁሉ ከሕዝብም ሁሉ ሰዎችን ዋጅተህ ለአምላካችን መንግሥትና ካህናት ይሆኑ ዘንድ አደረግሃቸው፥ በምድርም ላይ ይነግሣሉ እያሉ አዲስን ቅኔ ይዘምራሉ።
11 አየሁም፥ በዙፋኑም በእንስሶቹም በሽማግሌዎቹም ዙሪያ የብዙ መላእክትን ድምፅ ሰማሁ፤ ቍጥራቸውም አእላፋት ጊዜ አእላፋትና ሺህ ጊዜ ሺህ ነበር፥
12 በታላቅም ድምፅ። የታረደው በግ ኃይልና ባለ ጠግነት ጥበብም ብርታትም ክብርም ምስጋናም በረከትም ሊቀበል ይገባዋል አሉ።
13 በሰማይና በምድርም ከምድርም በታች በባሕርም ላይ ያለ ፍጥረት ሁሉ በእነርሱም ውስጥ ያለ ሁሉ። በረከትና ክብር ምስጋናም ኃይልም ከዘላለም እስከ ዘላለም በዙፋኑ ላይ ለተቀመጠው፥ ለበጉም ይሁን ሲሉ ሰማሁ።
14 አራቱም እንስሶች። አሜን አሉ፥ ሽማግሌዎቹም ወድቀው ሰገዱ።
እግዚአብሔር ይመስገን አንተን ስለ ሰጠን ❤❤ እህት ወንድሞቼ Like አርጉት❤
ከቁጠ ሁሉ በኢየሱስ ያደናኝ እግዚአብሄር ይመስገን ❤ ዘመኖት ይበርክ ፀጋ ይብዘሎት ፓስተር ❤
ፓስተር የተናገርካቸው ነገር ሁሉ እውነት ነዉ እውነት ነው
Pastorye Geta Eyesus bebizu bebizu yibarkeh. Zemenih yibarek. Endinineka Geta anten sileseten simu yibarek.❤❤❤❤❤❤
ፓስተር እግዚአብሔር ይባርክህ ጽጋ ይብዛልህ በዚህ ዘመን ጌታ እናንተን ለምልክት ስላስፐምጥልን እግዚአብሔር ክብሩን ይውሰድ❤❤❤❤
በምዕራፍ በምዕራፍ ማስተማርህ መልካም ነው እጅግ ጠቃሚ ነው ተባረክ !!!!!
የቆዩ መዝሙሮች በጣም የማይጠገቡ ❤❤❤❤❤
You are blessed ❤❤❤❤❤❤❤❤❤❤❤❤❤❤🎉🎉🎉
God bless you and your family pastor asfaw 🙏🙏🙏👍
ሰላም ላንተ ፓስተርዬ የሚገርም ነው እግዚአብሔር በትልቅ ቤተክርስቲያን በነበርኩበት ይናገርነበር በ3 ነገር አዝኛለው አለን 1በሚፈሰው ደም 2የንፁሃን እንባ 3በብዙዎች ላብ የሚቀልዱ ህዝቤ ግን እየቀጣኋቸው አልገባቸውም ምንም አልመሰላቸውም አለ ንስሃ አንግባ ስለምድራችን በቅዱሳኑ ስለሚሰራው ግፍና ሃጢአት
God bless you and your family ❤❤❤ thank I can get so many information about end of the year❤❤❤❤
አሜን አሜን አሜን ተባረክ ፓስተርዬ የኔ አባት❤❤❤❤❤
እዉነት ነዉ ኢየሱስ ብለን ስንኮምት መናፍቅ ይሉናል። ኢየሱስ ጌታ ነዉ በማለታችን መናፍቅ ካስባለን አሹ ደስ ይላል።
@@Alemtsehay777 እውነት ነው እኔ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ዲያቆን ነኝ ግን በጌታ ስም ፣ኢየሱስ ኢየሱስ ስል መናፍቅ ይሉኛል።
አንድኛህን ወዲያ ለቀህ ቤተ ክርስቲያንን ሂድልን ይሉኛል የሥራ ባልደረቦቼ
ግን ደስ ይለኛል ምክንያቱም በሰማይ ሽልማት የሚያስገኝ የሚያስመሰግን ነው የጌታ ስም ክብር ለአብ፣ለልጁ፣ለመንፈስ ቅዱስም ይሁን።
ደስ ይበልሽ
@@deaconabrham የኔ ወንድም አዎ የኢየሱስ ስም ስንጠራ መናፍቅ የማርያም ጠላት ይሉናል። እኛ የወንጌል አማኝ የጌታችን እናት ማርያም አይደለም እሷን መጥላት የሚጠላንን ጠላታችን ራሱ እንወዳለን ምክንያቱም ኢየሱስ የሚጠላችሁን ዉደዱ ብሎ አስተምሮናል። ወዳጄ እግዚአብሔር ፀጋዉን ያብዛልህ። ክርስቶስ ብለህ ጀምረህ ክርስቶስ ብለህ ጨርስ።
@@Alemtsehay777 አሜን ማርያምን መውደድ ማለት ርሷን ከኑሮዋ ሁናታዋ ንግግሯ መማር ነው።
ንግግሯ ደግሞ መድኃኒቴ ያለችው፣ርሱን ስሙት ያለችውን ጌታን ብቻ መስማት ነው።
@@deaconabrham አዎ ትክክል። እሷም የወንጌል አማኝ ነች። ከሐዋሪያቶች ጋር ተግታ የምትፀልይ ጀግና ሴት ነች።
🕊⚓️🐑🙏🏽🏃🏾♂️
ይህ የሃሳዊ ክርስቶስ ይዟት ሚመጣው ምልክት ግራ የተገባው የጴንጤው እምነት
ተባረክ,ፓስተር,ረጅም,ዘመን,ጤና,ከእነቤተሰብህ,ይሁንልህ,ጌታ,ክብሩን,ሁሉ,ይውሰድ
Egziabiher yibarikih wendime paster Asfaw.
የእግዚአብሔር ሰጦታ ኖት ንፁህ ወንጌል ሰለምታሰተምሩ።
Paster God bless you
ጌታ የሱስ አብዝቶ ይባርክህ 🙏 ፓሰርየ, በጣም አንወድሃለን, በጣም አየተኸምከን ነው, ኑርልን. ጌታ ረጅም አድሜ ይስትህ::🙏🙏🙏
ተባረክልን ፓስተር ፤አቤቱ ማረን አባ
ወንድሜ ተባረክ ፀጋውን የብዛልህ
Tebarek bebzu 🙏🙏🙏🙌🙌🙏🥰🥰
እግዚአብሔር ይባርክህ ፓስተር
ፓስተርዬ ተባረክህ ፀጋ ያብዛልህ እንወድሃለን❤❤❤❤❤
God bless you pastor!
የመደምደሚያችንን መጨረሻ በፀጋ ቃል ስላስተማከን ተባረክ❤❤❤❤❤❤❤
God Bless You
Tebareki
Amen amen
ጌታ ሆይ ማራናታ አሜንጌታ ኢየሱስ ሆይ ቶሎና
ፓስተር ስለመጨረሻዉ ዘመን ስለጀመርከዉ ትምህርት ጌታ ኢየሱስ አብዝቶ ይባርክህ፡፡ ትምህርቱ ራዕ. 9፡1-23 ድረስ ሂዶ ቆመ፤ በሰላም ነዉ ትምህርቱ የተቋረጠዉ? ምክንያቱም ቀጣይ ትምህርቶችን ከአንተ ዩቲዩብ ቻናል ላይ ፈልጌ አጣሁት፤ ተባረክ፡፡
ከሁለት ሳምንት በኋላ ይቀጥላል... ጌታ ቢፈቅድ
🎉🎉🎉
ዕብራውያን 11+24 መከራን እንደመረጠው የፈርዖንን ፕሪቭሌጅ እንደናቀዉ ሙሴ፤ በኛምዘመን ዓለምን ክዶእን እንዳሰመሰከረው እንደ ሙሉቀንመለሠ አብተው ከበደም ሌላኛው የዕምነት አርበኛ ☑️
እንደዚህ አይነት ትምህርት ስንማር ላይክ እያደረግን እንጀምር እይታ 4.2k ነዉ። ነገር ግን ላይክ 1000 እንኳ አልሞላም። why?
Are you fine!
ተበረክ ፓስተር በትምህርትህ ተበሪኬአለሁ ፣ ጥየቄ አለኝ:- ሐሰተኛ ክርስቶስ የምነሰው ከአሕዛብ ወይስ ከእስራኤል ??? ጥየቄው ስህተት ከሆና ይቅርተ አድርግልኝ
🎉🎉🎉
God bless you