ዘማሪ ዲያቆን አቤል መክብብ /Abel Mekibeb /ሚስጥረኛዬ ነሽ ❤️❤️❤️

Поділитися
Вставка
  • Опубліковано 8 лют 2025
  • ሚስጥረኛዬ ነሽ
    አውቀዋለሁ ደጅሽን የእረፍት ቦታዬን
    ጽኑ ሰላም ጸጥታ ማግኛዬን
    የት እሄዳለው አልልም ሲከፋኝ
    ኪዳነ_ምህረት አንቺ እያለሽልኝ/2/
    ከአጸደ መቅደስሽ ከስዕልሽ ስር
    እረፍቴ በዚያ ነው በቅዱሱ ደብር
    ከተራራው አናት ከደጅሽ መጥቼ
    ሰምሮልኛል ስምሽን ጠርቼ
    ሚስጥረኛዬ ነሽ ሚስጥረኛዬ
    ኪዳነ_ምህረት መፅናኛዬ /2/
    የሮማን አበባ መዓዛሽ ተወዳጅ
    በረከትን ልቅሰም ሳልለይ ካንቺ ደጅ
    አስራትሽ አድርጊኝ ጠቅልይኝ እናቴ
    ታብብልኝ ትፍካልኝ ሕይወቴ
    ሚስጥረኛዬ ነሽ ሚስጥረኛዬ
    ኪዳነ_ምህረት መፅናኛዬ /2/
    አጠገቤ ጎኔ በዙሪያዬ እንዳለሽ
    እንደርሱ ነው ልቤ እማ የሚያወራሽ
    አልቅሼ ሲቀለኝ ነግሬሽ የውስጤን
    አትዘገይም ስትሠሪልኝ ቤቴን
    ሚስጥረኛዬ ነሽ ሚስጥረኛዬ
    ኪዳነ_ምህረት መፅናኛዬ /2/

КОМЕНТАРІ • 3