አል-በቀራህ | (ክፍል-13) {አያ 88-96} | ተፍሲር | በሸይኽ ሙሐመድ ሓሚዲን || Tefsir | by Sheikh Mohammed Hamiddin
Вставка
- Опубліковано 31 жов 2024
- ሸይኽ ሙሐመድ ሓሚዲን ሐገራችን ኢትዮጵያ ካፈራቻቸው ብርቅዬ የእስልምና ኃይማኖት አዋቂያንና መምሕራን መሐከል በቀዳሚነት ከሚጠቀሱት ውስጥ አንዱ ናቸው።
በኢትዮጵያውያን ሙስሊሞች የዳዕዋ እንቅስቃሴ ላይ በጉልህ የሚታይ አሻራቸውን ያኖሩ፣ ተወዳጅነትን ብሎም ተቀባይነትን ያገኙ የእውቀት ባልተቤት ናቸው።
በተለይም ቁርኣንን በመፈሰሩ(በማብራራቱ) ዘርፍ ላይ ያላቸውን ድንቅ ብቃት በዘርፉ ላይ ካደረጉት ተሳትፎ አኳያ በቀላሉ መረዳት ይቻላል። አዲስ አበባ በሚገኘው ፈትህ አባቦራ መስጂድ ለዓመታት የአላህን ቃል ቁርኣን በመተርጎምና በማብራራት ለአካባቢው ማ/ሰብ እውቀትን እየመገቡ ከመቆየታቸውም ባሻገር፣ በካሴትና በተለያዩ ማሰራጫ መንገዶች ለመላው አድማጮቻቸው እያደረሱ ቆይተዋል።
አሁን ደሞ ጀሞ ሁለት አካባቢ በሚገኘው ሰዒድ ያሲን መስጂድ ውስጥ በተሻሻለ ሁኔታ ትምሕርታቸውን እያደረሱ ይገኛሉ።
ሱና መልቲሚዲያም አድማጭ ተመልካቾችን በሚመጥን መልኩ በጥራት ለውድ ቤተሰቦቹ በማድረስ ላይ ይገኛል።
ያላችሁን ማንኛውንም ሐሳብና አስተያየት አድርሱን።
ቻነላችንንም ሰብስክራይብ በማድረግና የደወል ምልክቷን በመጫን መሰል ፕሮግራሞችን በቀላሉ ማግኘት ይችላሉ።
ቪዲዮዎቻችንን ከወደዳችሁ፣ ላይክና ሼር፣ ያላችሁን አስተያየት ደሞ ኮሜንት በማድረግ እንድታሳውቁን በአክብርዎት እንጠይቃለን።
"ጉዟችንን ከሥንቅ ጋር!"
©ሱና መልቲሚዲያ
#ተፍሲር #Tefsir #Al_Baqarah #አል_በቀራህ
ጀዛኩሙላህ ኸይር ያሸይኽ
ጀ ዛ ከ ላ ህ ር
Jezakallah keyiren sheh
ጀዛኩሙሏሁ ኸይር ያሸኹና
አህለን ኡስታዝ አላህ ይጥብቃቹ
ጀዛኩሙላህ ኸይር
የሽህ አላህ ይጠብቃችሁ
ጀዛኩም አላሁ ኽይርን
ጀዛኩሙላህ ኸይር ጀዛ አልልህ ይጠብቀን ከጥመት ወንጀላችንን ሁሉ ይቅር ይበለን ከመልካም ሰሪወችም ያድርገን
Jazakumolah wakar Allah yixabiqih
ጀዛከአላሁ ኸይረን
ጀዛኩም አለህ ከይር ሹኩና በሰማነው ተጠቃሚ ያረገን ያረቢ
ጀዛኩሙላህ
👌👌👌👌👌👌👌👌ጀዛኩምላሁ ኸይረን
Subhan Allah
Yaa Allah Tikikilegna Amagnoch Adirgen
ማሻአላህ ሼክ አላህ እድሜና ጤና ይወፍቃቹ አላህ ያቆይልን
Aslmalkum. Mashalla.sahk
😘
አሠላሙአለይኩምወራህመቱላሂወበረካትሁአላህእእእረጂምእዲሜይሥጥልንሺህአቺንንንንለዘላለምኑሩልንንየሙሥልሙብርሀንናቺቺቺቺቺቺቺቺሁሁሁሁሂሂ
አላህ ሆይ ረመዳችንን ተቀበለን
አላህ ዱአችንን ተቀበለን
አላህ ሆይ ቂያማችንን ተቀበለን
አላህ ሆይ ቂራታችንንንን ተቀበለን
ወንጀላችን ማረን
መልካም ስራችንን ተቀበለን
ኢስልምናንና ሙስሊሞችን የበላይ አድረገን ያረብ
ሸኻችን እድሜዎት ያርዝምልን ምንዳዎት ጀነት ይሁን 💕
ውድሙስልምእህትወድሞቼሰብስክራይብአርጉኝ
ኡለማወቻችን የኡማው ብርሃን የነብያት ወራሽ ኑሩልን የእኛ እንቁወች
አይ የኛ ነገር በካፍሮች ፔጅ በሽሆች ሼር ለይክ ይደረገል በተረ ወሬ በድናቺና በቁርኣን ተፍስር ለይ ማንም የያውም ዬለም አጂብ!!
የጀመዓ ክፍል 14 አለገኛውትም እስት የያቹ ልንኩን ስጡኝ
አላህ ኢዱኒ አኼራህን አላህ ያሳምርለወት ያረብ አንድበቱ ጣፋጭ ስወዳችሁ
ያአላህ አመለጠኝ
አህለን ውስታዝ አላህ ሀያቶን ያቆይልን ላአላህ ብዬ እወዶታለው
ጀዛ ኩምላህ ኸይር
አህለን ውዱ ሸኻችን ጀዛኩሙላህ ኸይር ረጂም እድሜና ክብር ለኦለሞች እና ለወላጆች አብዝቶ ይስጥልን
ጀዘኩም አለሁ ከይር
ክፍል 14. አልተለቀቀም ነው
ለገኘው አልቸልኩም
በአለህ የሚትፕቁ ጡቁሙኝ
Jezakallah ustazana
أحسن الله إليكم وجزاكم الله خيرا شيخنا الفاضل لله يحفظكم ويطول عمركم يارب. اللهم اجعل القرآن ربيع قلوبنا ونور صدورنا ياارحم الرحيمين
جزاكم الله خير
ጀዛካላህ ኸይር ሸህ
ጀዛኩም አሏህ ኸይር ምስጋና ለአለማቱ ጌታ ነገሮችን. አመቻችቶ ላገናኘን الحمدالله
ጀዛኩም አላህ ከይር ሸኩና በሰማነው ተጠቃሚ ያርገን ቁራአንን ከነ ማአል ትርጉሙ ያረቢ ምንኛ መታደል ነው
ሁላቹም ላይ አድርጉ
አላህ ለይለተል ቀድርን ይወፍቀን
ua-cam.com/video/MS2hEu0ONgY/v-deo.html
ይቅርታ እንዳትተጠይቁ ሊጠይቁ ነው ያለውን ካፊር ግን ሙስሊሞች እንደዋዛ አትለፉት በስም አጥፊና በሀሰተኛ መረጃ መከሰስ አለበት
As wr wb down load indnaderg bita mechachulin
🤚 አሰላሙአለይኩም ወራህመቱላሂ ወበረካትሁ🤚
~~~~~~~~~~~~~~~~~~~~~~~~~
*ለይለቱል ቀድር*
~~~~~~~~~~~
#ጥያቄ፡ ያለሁበት ለሊት ለይለቱል ቀድር መሆኑን እንዴት ማወቅ እችላለሁ? ይህን የተከበረ ለሊት እንዴትስ ላሳልፍ? ሶላት በመስገድ ወይስ ቁርአን በመቅራት?
-------------------
#መልስ፡ ቢስሚላሂ ረህማኑ ረሒም
•ለይለቱል ቀድርን (የውሳኔዋን ለሊት) ህያው ማድረግ እንደሚወደድ የሚጠቁሙ ብዙ ሐዲሶች ተዘግበዋል። የአላህ መልእክተኛ (ሰ.ዐ.ወ) እንዲህ ይላሉ፡-
”من قام رمضان إيمانًا واحتسابًا غفر له ما تقدم من ذنبه “ ”ومن قام ليلة القدر إيمانًا واحتسابًا غفر له ما تقدم من ذنبه“
“(የአላህን ቃልኪዳን) እያመነና (ምንዳውን) እየተሳሰበ በረመዳን ለሊት የቆመ (የሰገደበት) ሰው ያሳለፈውን ወንጀል በሙሉ ይማራል።” “(የአላህን ቃልኪዳን) እያመነና (ምንዳውን) እየተሳሰበ ለይለቱል ቀድርን የቆመ (የሰገደበት) ሰው ያሳለፈውን ወንጀል በሙሉ ይማራል።” (ቡኻሪና ሙስሊም ዘግበውታል)
•ለይለቱል ቀድር የተባረከ ለሊት ነው። አላህ ወህይ (ራእይ) ለማውረድ መርጦታል። አላህ እንዲህ ይላል፡-
حم * وَالْكِتَابِ الْمُبِينِ * إِنَّا أَنزَلْنَاهُ فِي لَيْلَةٍ مُّبَارَكَةٍ إِنَّا كُنَّا مُنذِرِينَ
“ሐ.መ (ሓ ሚም)፡፡ አብራሪ በኾነው መጽሐፍ እንምላለን፡፡ እኛ (ቁርኣኑን) በተባረከች ሌሊት ውስጥ አወረድነው፡፡ እኛ አስፈራሪዎች ነበርንና፡፡” (አድ-ዱኻን 44፣ 1-3)
•አላህ በዚህ አንቀፅ ውስጥ በመፅሀፉ (በቁርአን) ይምላል። በተባረከ ለሊት እንዳወረደውም ይናገራል። ይች ለሊትም ለይለቱል ቀድር ናት።
•ለይለቱል ቀድር የተለያዩ ምልክቶች አሏት። በርሷ ውስጥ ሙስሊሞች የሚጠመዱባቸው የተለያዩ ሥራዎችም አሉ። በዚያ ቀን የሚሠሩ አምልኮዎችም ሌላ ጊዜ ከሚሠሩት ይበልጥ የላቀ ክብርና ደረጃ ያስገኛሉ።
•ከለይለቱል ቀድር ምልክቶች መሀል የተወሰኑትን እንጥቀስ። ኢማም ኢብኑ ተይሚያህ ፈታዋ አል-ኩብራ ላይ እንዲህ ይላሉ፡-
“ለይለቱል ቀድር ከረመዳን የመጨረሻው አስር ቀናት ላይ የሚከሠት አንድ ለሊት እንደሆነ ከነብዩ (ሰ.ዐ.ወ) ተነግሯል። ‘ከረመዷን ወር የመጨረሻዎቹ አስር ቀናት ውስጥ ነው ያለችው።’ ብለዋል፤ ነብዩ (ሰ.ዐ.ወ)። በአስሩ የረመዷን ወር የመጨረሻ ቀናት በነጠላ የሚቆጠሩት ቀናት ላይ እንደሆነችም የሚጠቁሙ ሐዲሶችም እንዲሁ ተዘግበዋል። ነጠላነት ግን ካለፉት የረመዳን ቀናት ወይም ከሚቀሩት የረመዳን ቀናት አንፃር ሊታይ ይችላል። ስለዚህ ካለፈው አንፃር ካየነው ሀያ አንደኛው፣ ሀያ ሦስተኛው፣ ሀያ አምስተኛው፣ ሀያ ሠባተኛው እና ሀያ ዘጠነኛው ቀን ይበልጥ ለይለቱል ቀድር ሊሆኑ እንሚችሉ ይጠረጠራሉ። እነዚህ ብዙዎች የሚጠብቁበት አቆጣጠር ነው። ይሁንና የቀሩትን የረመዷን ቀናት በማሰብ ልንቆጥርም እንችላለን። ምክንያቱም ነብዩ (ሰ.ዐ.ወ) እንዲህ ይላሉ፡-
لتاسعة تبقى لسابعة تبقى لخامسة تبقى لثالثة تبقى
“እርሷ በሚቀሩት ሰባት፣ አምስት፣ ሦስት… ቀናት ውስጥ ትሆናለች።”
•በዚህ መሠረት ወሩ ሠላሳ ቀን ከሆነ ከታች ወደ ላይ ሲቆጠር ጥንድ ቀናት የሚሆኑት ለሊቶች ከላይ ወደ ታች ሲቆጠር ለይለቱል ቀድር ሊሆኑ ይችላሉ። ማለትም ሀያ ሁለተኛው ለሊት ዘጠኝ ቀናት የሚቀሩት ለሊት ሊሆን ቻለ። ስለዚህ ሀያ አራተኛው ቀን ደግሞ ሰባት ቀናት የሚቀሩት ለሊት ሆነ… እያልን ልንሄድ ነው። ታላቁ ሶሐባ አቡ ሰዒድ አልኹድሪይ (ረ.ዐ)- በሶሒሕ እንደተዘገበው- ያለፈውን ሐዲስ በዚህ መልኩ ተረድተውታል።
•በዚሁ መሠረት ወሩ በሀያ ዘጠኝ ካበቃ ደግሞ ሒሳቡ ከዚህ በፊት ከተጠቆሙት ቀናት ጋር ተመሳሳይ ቀናት ላይ ለይለቱል ቀድርን ልንጠብቅ ነው ማለት ነው። ስለዚህ ሙስሊም ሁሉ የመጨረሻዎቹ አስር ቀናት ውስጥ ለይለቱል ቀድርን በሙሉ ንቃት መጠበቅ ይገባል። የአላህ መልእክተኛ (ሰ.ዐ.ወ) “አስሩ የመጨረሻ ቀናት ላይ በንቃት ጠብቋት!” ብለዋል። በተለይም የመጨረሻዎቹ ሰባት ቀናት ላይ መጠበቁ በጣም ይጠነክራል። በተለየ ሁኔታ ደግሞ ሀያ ሰባተኛው ለሊት እንደሆነች ኡበይ ኢብኑ ከዕብ (ረ.ዐ) ይነግሩናል። ‘እንዴት አወቁ?’ ተብለው ቢጠየቁ ‘ነብዩ (ሰ.ዐ.ወ) በነገሩን ምልክት ነዋ። የእርሷ (የለይለቱል ቀድር) ንጋት ላይ ፀሀይ ልብስ እንደሚታጠብበት ሳፋ (ጠሽት) ንፁህና ደካማ ሆና ትወጣለች። ሲሉ መልእክተኛው ነግረውናል።’
•ኡበይ ኢብኑ ከዕብ ከነብዩ (ሰ.ዐ.ወ) ይዘው የነገሩን ይህ ምልክት የታወቀ የለይለቱል ቀድር ምልክት ነው። ለሊቷ መሀለኛ የአየር ሁኔታ ያላትና ብርሀን ያላት መሆኗ ሌሎች ምልክቶች ናቸው። በእርግጥም አላህ ለአንዳንድ ሠዎች በመናም (በህልም) ሊያሳውቃቸውና ብርሀኗን ሊያሳያቸው ይችላል። ይህ ለይለቱል ቀድር ነው ብሎ የሚነግራቸው ሠው ሊልክባቸው ወይም ልቡን ከፍቶለት እውነት ለይለቱል ቀድር መሆኗን የሚለይበት ነገር ልቡ ውስጥ ሊጥልበት ይችላል።” የኢብኑ ተይሚያህ ንግግር እዚህ ላይ አበቃ።
•በእለቱ የሙስሊሞች ሥራ ምን መሆን አለበት?
•ለሊቱ የተባረከ ለሊት ነው። ከአንድ ሺህ ወራት በላይ ዋጋ ያለው ለሊትም ነው። አላህ -ልክ ጁምዓ ውስጥ ያለችውን፣ ዱዓ ተቀባይነት የሚያገኝባትን ውድ ሰዓት እና ታላቁን ስሙን (ኢስሙል አዕዘምን) እንደደበቀ ሁሉ- ለይለቱል ቀድርንም ደብቋታል። የመደበቃቸው ምስጢርም ሠዎች እነሱን ለማግኘት እንዲጥሩ ለማድረግ ነው። በእርግጥ ለይለቱል ቀድር መች እንደሆነ በውል ባይታወቅም አስሩ የመጨረሻ ቀናት ውስጥ መሆኑን አሳልፈናል። ስለዚህ እርሷን ለማግኘት አስሩን የመጨረሻ ቀናት ለሊቶች በሙሉ በዚክር፣ በዱዓ፣ ቁርአን በመቅራት፣ ሶላት በመስገድ… ማሳለፍ ያስፈልጋል።
•የአላህ መልእክተኛ (ሰ.ዐ.ወ) አስሩ የመጨረሻ የረመዳን ቀናት ውስጥ -ከምንም ጊዜው በላይ- ለዒባዳ ይጠነክራሉ። ቁርኣን ያነባሉ። ሶላት ያበዛሉ። ዱዓ ላይ ይጠነክራሉ። ቡኻሪ እና ሙስሊም አዒሻን (ረ.ዐ) ዋቢ በማድረግ እንደዘገቡት:-
أن النبي صلى الله عليه وسلم كان إذا دخل العشر الأواخر أحيا الليل وأيقظ أهله وشد المئزر
“የአላህ መልእክተኛ (ሰ.ዐ.ወ) አስሩ የረመዳን የመጨረሻ ቀናት በሚገቡ ጊዜ ለሊቱን ህያው ያደርጋሉ። ቤተሰቦቻቸውን ያነቃሉ። ሽርጣቸውን ያጠብቃሉ።”(ቡኻሪና ሙስሊም ዘግበውታል)
"አላህ ለይለተል ቀድርን ወፍቋቸው ተጠቃሚ ከሚሆኑት ባርያዎቹ ያድርገን አላሁማ አሚን🤲
السلام عليكم ورحمةالله وبركاته
ሱናዎች እንዴት ናቹ
አላህ በሚትሰሩት መልካም ስራ ከሰባቹት ከሰራቹት በለይ ምንደ ይስጣቹ አሚን
በመቀጠል አስተየት አለኘ አስተየቴ የሚሆነው በተፍሲር ዙሪያ ነው ተፍሲሩ እጅግ ማራኪ አጓጊ ጠፋጭ ነው ግን ግዜ ለእኛ ለኢትዮጵያ ለለን ሰዎች ለመከተተል አመቺ አይደለም ማለቴ ቲቪ አፍሪካ ለይ ሰኣቱ ሁለቱም አይመችም ከሊሊቱ 6 ሰኣት እንቅልፉን ትቶ ማንም አይቀመጥም ለምን ጠዋት ስራ ስለለበት ይተኛል እና ሱሁር ሰኣት ማን ተነስቶ ይከተተላል ስለዚ ሰኣቱ ቢስተካከል እለለው
ሌላው እዚህ ሼር የሚተደርጉትን ደዉንሎድ አድርገን ለመስማት የኔት ችግር አለ ከቻለዙቹ አፐሊኬሽን ወይም የለ ኔት የሚንጠቀምበት መንገድ ቢኖር እለው ከጠፋው ይቅርታ ጀዛኩሙላሁ ኸይራ
ኧረ ወንድሞች background ነሺዳውን በአላህ ተውት: ቁርአን ተፍሲር ጋር አብሮ አይሄድም በዛ ላይ ቀረፃው በጣም ጥራት አለው ምንም አያስፈልገውም! እባካችሁ
ነሺዳ ካላስገቡ ደማቸው አይስራም ስንት ፕሮግራም መስማት እየፈለግን እጉርጉሮ ያስገቡበታል
@@እሙዙመራ እውነት ነው እህቴ በጣም ብዙ ኘሮግራሞች በነሺዳ እና እንጉርጉሮ ምክንያት ማዳመጥ አቅቶኝ አቋርጫለሁ
አሁን መች በደንብ ይሰማል ወይ ሁሌ አይብ ካላወጣቹ አይሆንም አንቺ ትኩረትሽን ት/ት ላይ አርጊ
@@rebubintbilal4678 ለምን አስፈለገ እጉርጉሮ
@@rebubintbilal4678 ነሺዳው ስለረበሸን እኮ ነው ረበሸን ያልነው!! ላንቺ ካልረበሸሽ ለሌላውም አይረብሽም ማለት አይደለም!! ከራስሽ ብቻ አይተሽ አይብ ካላወጣችሁ ምናምን ትያለሽ እንዴ?? በቃ ላንቺ አልረበሸሽም አይደል? ዝም በይ። እኛ ደሞ ረበሸን ተናገርን፣በመናገራችን ደሞ አላህ ይስጣቸው የመጨረሻውን ክፍል ያለ እንጉርጉሮ ፓስት አደርገዋል
ነሺዳና እንጉርጉሮ ለታፍሲር እንኳን ይቅር እስኪ:-( እናነተ ስለወደዳችሁት አድማጭ ይወደዋል ማለት አይደለም
ጀዛኩሙሏህ ኸይር ያሸይኽ
ጀዛኩሙላሁ ኸይረን ጀዛ ሸይኹና
Subhan allah
ማሻ አሏህ
ጀዛኩም አላህ ኸይር ያሼህ