እጅግ ውብ መልከአምድር አቅማመጥ መንዝ ጓሳ ጥብቅ ስፍራ ሰላም ለኢትዮጵያ ሰላም ለሀገራችን አሴ ዓዋዜ Ase Awaze ፫/፩/፳፻፲፬ ዓ/ም
Вставка
- Опубліковано 5 лют 2025
- #Ethiopian_Turist_Destnation #መንዝሸዋ #አሴዓዋዜ
እጅግ ውብ መልከአምድር አቅማመጥ መንዝ ጓሳ ጥብቅ ስፍራ ሰላም ለኢትዮጵያ ሰላም ለሀገራችን አሴ ዓዋዜ Ase Awaze ፫/፩/፳፻፲፬ ዓ/ም
መንዝ ማለትም ደሙን የረጨበት ስለሆነ ነዝሃ መንዝ ተባለ ፡፡
ቅዱሱ ጽዋም እዚችው ምድር ሲገኝ ብዙ ምስጢራት ስላላት ከዚህ በላይ መናገር አልችለም ፡፡በጣምም ቅዱስ ስፍራ ነው ፡፡
መንዝ ጓሳ በአማራ ክልል ሰሜን ሸዋ ዞን ከአዲስ አበባ በ265 ኪ.ሎ ሜትር ርቀት ላይ በመንዝ ጌራ ወረዳ የሚገኝ ስፍራ ነው፡፡ ከ17ኛው ክፍለ ዘመን ጀምሮ በአካባቢው ህብረተሰብ በመጠበቅ ላይ ያለው ደጋማው የመንዝ ምድር መገለጫ የሆነው የጓሳ አካባቢ በጓሳ ሳርና በመልከዓ ምድሩ ይበልጥ ሲታወቅ ዛሬ ላይ ደግሞ ስነ-ምህዳሩ ያስጠለላቸው ብርቅዬ ዱር እንስሳትና አእዋፋት መለያዎቹ ሆነዋል፡፡
የመንዝ ጓሳ መልከዓ ምድር አቀማመጡ እጅግ ውብና ማራኪ፣ የማህበረሰቡ አኗኗር ፣ ልብን የሚገዙ የአዕዋፋ ዝርያዎች፣ ጭላዳ ዝንጀሮ ፣ቀይ ቀበሮና የተለያዩ የእንሰሳትና ዕፅዋት መገኛ በመሆኑም ከቱሪስት መዳረሻነቱ በተጨማሪ የአዋሳኝ ወረዳዎች፣ የአባይ፣ የአዋሽንና ታላቁ የስምጥ ሸለቆ የውሃ ክምችትን ለመቆጣጠር የሚያስችል የከርሰ ምድር ውሃ ባለቤትና የብዝሀ ህይወት መገኛ በመሆኑ ለሳይንሳዊ ጥናትና ምርምር ማዕከልነት ግልጋሎት እየሰጠ ያለ ቦታ ነው፡፡
መንዝ ጓሳ ማህበረሰብ አቀፍ ጥብቅ ስፍራ ለዘመናት የነበረውን እምቅ የተፈጥሮ ሀብት ሸሽጎ የኖረ አካባቢ ሲሆን በፍራንክፈርት ዙ ኦሎጂካል ሶሳይቲ መንግስታዊ ያልሆነ ተቋም አማካኝነት ሰፊ ስራ ተሰርቶ ይህ የተፈጥሮ ችሮታ ወደ ቱሪዝም አቅም ያደገበት ወቅት ላይ አንገኛለን፡፡ መንዝ ጓሳን ከዓለም ጋር በማስተዋወቁ ረገድ ተቋሙ ከፍተኛ ሚና የተጫወተ ሲሆን በስፍራው የጀመረው ፕሮጀክት በርከት ያሉ ተግባራት የነበሩት ሲሆን በዋናነት ማህበረሰብ አቀፍ አካባቢ ጥበቃና ቱሪዝም ተቀናጅተው ይህ ምድሩን ሲጠብቅ የኖረ ማህበረሰብ ከጠበቀው ምድር በሚስማማ ኢንዱስትሪ ኢኮኖሚያዊ ጠቀሜታ እንዲኖረው ማድረግ ነበር፡፡ በዚህ እቅድ ስኬትም መንዝ ጓሳና ፋና ወጊው ፍራንክፈርት ዙ ኦሎጂካል ሶሳይቲ በአዘርባጃኑ ዌስተርን ዩንቨርስቲ ዓለም አቀፍ ሽልማት ተቀናጅተዋል፡፡
መንዝ ጓሳ በሀገራችን ህግ የወጣለት የመጀመሪያው የማህበረሰብ ጥብቅ ስፍራ ነው፡፡
Guassa Community Conservation Area, located along one of the most significant historic routes in Ethiopia, offers spectacular Afromontane landscapes on the Guassa Plateau.
Trek on foot or on travel by mule to experience Ethiopia’s unique natural and culture heritage and traditional village life in the Ethiopian highlands. Discover breathtaking views bursting with endemic birds and mammals such as the iconic Ethiopian wolf and the charismatic gelada.
መንዝ ጌራ ምድር መሐል ሜዳ
መንዝ የሚለው ስያሜ የመጣው ከግዕዝ ቃል ሲሆን ትርጉሙና አመጣጡም መንዛት መርጨት ከሚለው ቃል የመጣ ሲሆን ሊቀ መልዐክቱ ቅዱስ ዑራኤል የጌታችንን ደም የረጨባት የምድር ማዕከል ናት ፡፡
መንዝ ማለትም ደሙን የረጨበት ስለሆነ ነዝሃ መንዝ ተባለ ፡፡
ቅዱሱ ጽዋም እዚችው ምድር ሲገኝ ብዙ ምስጢራት ስላላት ከዚህ በላይ መናገር አልችለም ፡፡በጣምም ቅዱስ ስፍራ ነው ፡፡
መንዝ በሰሜናዊ ሸዋ የሚገኝ ክፍል ሲሆን በውስጡ ላሎ ምድርን በስተደቡብ፣ ጌራ ምድርን በስተሰሜንና ማማ ምድርን በመካከል ይዞ ይገኛል[1] ። የመንዝ ድንበር በ3 ወንዞችና በአንድ ተራራ እንዲህ ይካለላል፦ ሞፋር ወንዝ (ደቡብ)፣ አዳባይ ወንዝና ወንጭት ወንዝ (ምዕራብ)፣ ቀጨኔ ወንዝ (በሰሜን) እንዲሁም በስተምስራቅ ከቆላው ኤፍራታ፣ ግድምና ቀወት የሚለየው የተራራ ሰንሰለት ናቸው [2] ።
መንዝ ለመጀመሪያ ጊዜ በታሪክ ተጠቅሶ የሚገኘው በቀዳማዊ አጼ አምደ ጽዮን ዜና መዋዕል ሲሆን በጊዜው መንዝሔል ይባል ነበር [3]። ቀጥሎም በአጼ በእደ ማርያም ዜና መዋዕል ተጠቅሶ ይገኛል [4] ።
መንዝ በኢትዮጵያ ታሪክ ውስጥ ቁልፍ ቦታ የያዘው በ17ኛው ክፍለ ዘመን መጠናቀቂያ፣ በነጋሲ ክርስቶስ ነበር። የመንዝ ተወላጁ ነጋሲ የአጋንጫ ኪዳነ ምህረትን ቤተክርስቲያን በመመሰረት ሲታወቅ የፍሩክታንም ደብር በማስፋፋት ይጠቀሳል። ነጋሲ ታላቁ እያሱን ለመጠየቅ በሄደበት በትክትክ በሽታ ሲያርፍ ልጁ ሰባስቲያኖስ ሸዋን ከመንዝ ሆኖ ያስተዳድር ነበር። ኋላ ላይ የተነሱት ንጉስ አብይ፣ ምንም እንኳ እናታቸው ከላሎ ምድር የመጣች ብትሆንም መስተዳድራቸውን ከመንዝ ወደ ሐር አምባ በማዛወራቸው የመንዝ ማዕከላዊነት ደበዘዘ። የሆኖ ሆኖ መንዝ ለሚቀጥሉት ዘመናት ታዋቂ መሪወችን በማፍራትና በማስተናገድ ትታወቃለች። ለምሳሌ የነጋሲ ዘር የሆነው መርድ አዝማች አስፋ ወሰን በ18ኛው ክ.ዘመን መጨረሻ ጠላቶቹ ሲያሳድዱት በፍሩክታ ኪዳነ ምህረት እንደተጠለለ ይነገራል። የንጉሥ ሣህለ ሥላሴ እናት ወይዘሮ ዘነበወርቅ፣ የነጋሲ ዘር ሲሆኑ ዋና ከተማቸውን በሰላ ድንጋይ፣ ላሎ ምድር መሥርተው ይኖሩ ነበር። እንዲሁም አቶ በዛብህ ("አባ ደቅር") የመንዝ ባላባት ሲሆኑ በዓፄ ቴዎድሮስ የአበጋዝ ሹም የነበሩና የአጠቃላይ ሸዋ አስተዳዳሪና ኋላ ላይ ከወደፊቱ ዳግማዊ ዓፄ ምኒልክ ሠራዊት ጋር በአምባ ዳየር ጦርነት አድርገው የተሸነፉ ናቸው። ቆይቶም ዓፄ ምንሊክ በአምባ አፍቃራ፣ መንዝ፣ ቤተ መንግሥትና የጦር መሣሪያ ግምጃ ቤት ገንብተዋል። በኋላ በጣሊያን ወረራ ወቅት ለነበረው ትግል መንዝ ማዕከላዊ ሚናን ተጫውቷል።
ባህላዊ መልክዓ ምድር
መንዝ እጅግ ለም የሆነ መሬት የሚገኝበት ሲሆን ጥሩ ዝናብ ሲገኝ በአመት እስከ 3 ጊዜ እህል ማጨድ ይቻላል። የአየር ጸባዩም፣ ከከፍታው አንጻር ደጋማ ሲሆን በደቡቡ ማማ ምድር የሚገኘው የአየር ንብረት ወይና ደጋማ ነው። ይህ ሆኖ እያለ የመሬቱ ተራራማ አቀማመጥ ከሞላ ጎደል በዚህ አካባቢ የሚደረግን ግብርና ከባድ ያደርገዋል።
በመንዝ የሚገኙ ቤቶች በባህር ዛፍ እና ጥድ የሚታጀቡ ሲሆን አቀማመጣቸውም ተሰባጥረው ነው። በሞላሌ የሚገኘው የቅዳሜ ገበያ እስከ 2000 ሰወችን ያስተናግዳል።
ከከፍታው አንጻር፣ ብዙው የመንዝ አካባቢ ብርዳማ ስለሆነ ልብስ የሚሰራው ከሪዝ (wool) ነው። ይህም ልብስ ባና ይባላል። እንጀራም ብዙ ጊዜ ከገብስ የሚጋገር ሲሆን የመንዝ ሰወች ውርጩንና ንፋሱን ለመከላከል ቤቶቻቸውን ከእንጨትና ጭቃ ይልቅ ከድንጋይ መሰራት ያዘወትራሉ። ከዚህ እና መሰል ባህላዊ ቅርሶች አንጻር በአካባቢው ህዝብ ዘንድ መንዝ «የአማራ ምንጭ» በመባል ይታወቃል።
የጓሳ ሜዳ በመንዝ የሚገኝ፣ወደ 110 ኪሎ ሜተር ስኩየር የሚጠጋ ስፋት ያለው፣ ከኢትዮጵያም ሆነ አፍሪካ ትልቁ የአፍሮ አልፓይን ስርዓተ ህይወት ቅሪት ነው። በዚህ ሜዳ 26 ምንጮች ሲኖሩ ቦታው ሳይታረስ ለ400 አመታት የተለያዩ ብርቅ እንስሳት (ምሳሌ፡- ጭላዳ ዝንጀሮ (200 የሚጠጉ) ፣ ቀይ ቀበሮ (ከ20 እስከ 50 ብቻ የሚደርሱ) ፣ አጋዘን፣ ወዘተ...) መኖሪያ በመሆን አገልግሏል። የአካባቢው ህዝብ የዚህን ጉዳይ መሰረት ሲያስረዱ፣ ከላይ የተጠቀሰው ጻዲቁ ዮሐንስ ምስራቃዊ በዚህ አካባቢ ሲኖር ሳለ አንዲት ሴት በውሸት አስረግዞኛል ብላ ከሰሰችው። የአካባቢውም ህዝብ ይህን ክስ ከጻዲቁ ፊት እንድትደግም አደረጓት እርሷ ግን ክሱን መድገም ብቻ አይደለም "ከዋሸሁ ድንጋይ ያድርገኝ" ብላም ጨመረች። በዚህ መሰረት ንግግሯን ሳታቋርጥ ወደ ድንጋይ ተቀየረች። ጻዲቁም በማዘን ሜዳው ምንም እህል እንዳያበቅል ተራገመ። በዚህ መሰረት በጥሩ ጤፍ ምርቱ ይታወቅ የነበረው ጓሳ የተለያዩ አውሬዎች መኖሪያ ሆነ።
በአሁኑ ወቅት በጓሳ ሜዳ 7 ኢትዮጵያ ውስጥ ብቻ የሚገኙ አጥቢ እንስሳት ይገኛሉ - ይህም ከአጠቃላዩ ኢትዮጵያ ብቻ ከሚገኙት አጥቢ እንስሳት 22.6% ነው። 111 የወፍ አይነቶች በመንዝ ሲገኙ ሰባቱ ኢትዮጵያ ውስጥ ብቻ የሚገኙ ናቸው።
am.wikipedia.o...%...
#ETHIOPIAN#መንዝ#አዲስዓመት#ጌራምድርመሐልሜዳ#SimienMountains#NationalPark.
#turismorecrear #turismo #visitindonesia #ehiopianews #visitafrica #turistas #travel #ethiopianentertainment #travelafrica #travelamerica #traveladdictgtv #musium #park #amazon #culture
አሴዋ ሰላም አሜን አሜን አሜን
Demesti buzume Ayesemame
እናመሰግናለን አሴ በጣም ያምራል🌻🌻🌻🌻
ያባቴን ሀገር እንዲህ እማምርምር መሆኑ እንደት ደስ ይላል እናመሰግናለን
Betam des yemile bota new wowww
አስዬ ወድሜ ሰላም ላተ ይሁን ወይ በጣም ደስ ይላል ከልብናመሰኛለን ወድማቺን ክበርልን አሜን አሜን አሜን ሰላም ለሀገራችንሰላም ለህዝባቺን ይሁን 😍💚💛❤🙏🙏
አሴዋ ደስ የሚል አረጓዲ ቦታ ስለምታሳየን እናመሰግናለን
ሰላም ሰላም ሰላም ለዚህ ቤት እግዚአብሔር ይመስገን አሜን አሜን አሜን እግዚአብሔር አገራችን ይጠብቅልን በጣም ደስ ሚል ቦታ ነው
ሰላምህ ይብዛልኝ አሴ ዋውውውውውው ቦታው ስያምር በጣም እናመሰግናለን ስላስጎበኜኤን
ዋዉዉዉዉ በጣም ያምራል አገራችን እኮ በጣም ያምራል እግዚአብሔር አምላክ ሰላምን ይመልስልን
Woow betam des yemil bota newu egzabiher Ethiopia agerachin selam yadergillen selamachin yemellisellen wandime barta
መንዜወች ለቃላቸው ሙትና ደግና እሩሁሩህነው
ኢትዮጵያ አገራችን ለምለሟ አቤት ማማሯ በጣም ደስ የሚል ቦታ ነው
ቦታዉ ልዩ ነው ደስ ሲል🇪🇹🇪🇹👍
አሴዬ ምርጥ እናመሰግናለን💝🌻💝🌻💝🌻💝🌻💝🌻💝🌻💝🌻💝💝🌻👍
በጣም እሚያምር ቦታ ነው ድንቅ ውበት 💚💛❤
በጣም የሚያምር ቪው ነው ወንድሜ እናመሰግናለን የናፈቀኝ ሀገሬን በጥቂቱም ስላሳየኧን
አሜን አሜን አሜን ትንሳዬ ዋን ያሳያን ፋጣሪ 🙏🙏🙏
በጣም ያምራል እናመሰግናለን 🙏
እናመሰግናለን አሲዬ ያምራል ሰላም ለኢትዮጵያ💚💛❤🙏🌻🌻🌻
እሴ ደግነህ
ጀበራ ይባላል❤️❤️❤️❤️❤️❤️❤️
Ethiopiyaye 💚💛❤️
Selam aa ensat nhke waoo!!!botouw betam yamirale
እሜን አሜን አሜን ሰላም ለሀገራችን አሴ በእውነት አለባበስህ አባቴ ከፊቴ መጣ ውይይይይይ ስደት አረ በቃ በለኝ አምላከ እስራኤል ።የዛፉ ስም ##### ጀምበራ ይባላል ###
አይዞን ገኒ ስሙን ግን ወጄልሻለሁ ጎበዝ🙏
በጣም የሚያምር ቦታ ነው 👍🙏
አሴ😍😍በርታልኝ አሪፋነው
ዋውውውው በጣም ዉብ ነዉ ቦታዉ አገሬ መንዝ ዉብ ነሽ እኮ
በጣም ያምራል አሴ
ዴስ የላል ቀጥልበት
ዋው በጣም ነው የሚያምረው ለሙዚቃ መሳሪያ ይውላል ያልከውን ግን ላውቀው አልቻልኩም ቦታው ግን ውብ ነው
Woww Sab like
ክላሲካው ደስ ሲል
ጎበዝ
ስምር ቦታው ክላሲካሉ ይመስጣል🌹🌹🌹
እንዲህ አይነት ስራዎች ሊበረታቱ ይገባል ሀገርን በማስተዋወቅ በኩል ትልቅ ድርሻ አላቸው
በጣም ደስይላል ወንድሜ በርታልኝ
ቢኒ ወንድምአለም እንዲህ ቀንጨብ አድርገን መጣን ስትሄድ ግን ብታጋራኝ ምናልባት በስራሕም ከሆነ የምትሔደው ይዘኸኝ ብትሔድ🙏
Asse I see Ethiopia inside of you. Thanks🙏
Thanks🙏
ሰላምህ በክርስቶስ ብዝት ይበልልን ውድ ወንድማችን ተፍጥሮ ድንቅ ነው በእውነት እደት እደሜያምር ደግሞ ደን አታጥፉ ክክክ ይሄ እደ ሸንበቆ ድምፅ እሚያውጣውን ዛፍ ወይይይይ ስውደው እጨውትበት ነበር
ግን በባድርው ተሳፍህ የት ደርስክ እኔ አሁ አሁ ውደላይ መጠክ እያልኩኝ ጋቤ አለባበስ ይብቃ ይከተት ሀሀሀሀሀ እውነትም ደገኛ ደገኛ ጠብቆኛ ላልቶ ይነበብልኝ
Zembaba new
wendm
ወንድሜ በርታ ድምፅህን አስተካክለው
እማ ሃገሬ እንዴት ያምራል 😍 አሥዬ እናመሰግናለን ቅርቅሃ አደለም እንዴ ዋሺንት እሚሆን
ክፋትን አሳየን
Asy woyo eskezari edite alfegne yegermal eskahun balmayeti yenafkgnen bota sisayhgne amesginalhu asy edite edemimir fetari hagerachinin selam yadergiln
አሴ አዎ ደረብረብ አድርገህ ብትለብስ ይሻልሀል እንጅ በዚህ ወፍራም ሰውነትህ ብርዱን አትችለውም ኪኪኪኪኪ ዋው አገሩ ግን በጣም ውብ ነው። እውነት ነው አሴ ግን ወደኛ ግድም ካሜራ አይወዱም ለምንድነው???
እናለማምዳቸው መሲ
እረ መንዝ የባቴ ጥሪቶች እዛ ናቸው እኔ ግን አላውቃቹውም
ያባቴ ጥሪቶች🤔 እንዴ እና ለምን አይፈለጉም ለማወቅ ማጠያየቅ
መንዝ የት ናችሁ መንዝ ማማ ወላ መንዝ ቃያ መዲያነለም መንዝ ማህል ሜዳ ዘመዶች እንደት ሆነው ይሆን ወኔ ሀገራችን እንደው እንደት ይሆን እስኪ ንገሩኝ የቅርብ ቤተሰቦች እዛ ናቸው
መንዝ መሐል ሜዳ ነን ድባቡ ቢያስፈራም አለን።
ጅብራ እራሱንጥሎ ክክክክክ
እንዲህ አይነት ስራዎች ሊበረታቱ ይገባል ሀገርን በማስተዋወቅ በኩል ትልቅ ድርሻ አላቸው